'' ለሁለንታዊ የሀገር እድገት ኢንዱስትሪዎች ጉ...

image description
- In Uncategorized    0

'' ለሁለንታዊ የሀገር እድገት ኢንዱስትሪዎች ጉልህ አስተዋፅኦ አላቸው''።

ቢሮው በተኪ ምርት ስትራቴጂ፣በኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ አምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ አገልግሎት ማዕቀፍ መመሪያ እና በአቅም ልማት ስትራቴጂ ዙሪያ ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ላሉ ዳይሬክተሮች፣አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲስጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያ መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ጃንጥራር አባይ ስልጠናው በሥራ ላይ ሊፈጠር የሚችልን ክፍተት የሚሞላ እና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን መሠረታዊ ችግር መቅረፍ የሚችል የድጋፍና ክትትል ሥርዓት እንዲኖር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጃንጥራር አክለውም ሰልጠናው ሙሉ የሚሆነው የሚደገፉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመሠረተ ልማት ችግሮች በመፍታት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እና የላቀ ውጤት ማምጣት ሲቻል እንደሆነ ገልጸዋል።

ለሁለንታዊ የሀገር እድገት ኢንዱስትሪዎች ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የጠቀሱት አቶ ጃንጥራር እንደ ሀገር የኢንዱስትሪዎች እድገት የተሻለ እና የማምረት አቅማቸው ውጤታማ እንዲሆን አመራሮች እና ባለሙያዎች በሙሉ አቅማቸው በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ችግር ፈች ቅንጅታዊ ሥራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments