የወረቀት አልባ ዲጅታል (Smart Office) አሰራር ያለ አስፈላጊ ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ አሰራርን ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡
የወረቀት አልባ ዲጅታል (Smart Office) አሰራር ያለ አስፈላጊ ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ አሰራርን ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማቀላጠፍ የወረቀት አልባ ዲጅታል አሰራር (Smart Office) ትግበራን ለማስጀመር እየሰራ ይገኛል፡፡ ቢሮዉ አሰራሩን ለማስጀመርም ለቢሮዉ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡
ስልጠናዉን ያስጀመሩት የምክትል ከንቲባ እና የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጃዉ ባይጨክን አሰራሩን ለመተግበር በቅድሚያ ዳይሬክተሮችን እና ቡድን መሪዎችን ማሰልጠን አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዉ ሰልጣኞች ስልጠናዉን በትኩረት መከታተል እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
አቶ ደረጃዉ አክለዉም የወረቀት አልባ ዲጅታል (Smart Office) አሰራር ያለ አስፈላጊ ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ አሰራርን ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የወረቀት አልባ ዲጅታል አሰራር (Smart Office) ትግበራን በተመለከተ በሁሉም የስራ ክፍሎች ላይ ክትትል እንደሚደረግና ሁሉም የስራ ክፍሎች አሰራሩን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
ሰኔ 14፣2016 ዓ.ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments